በዘንድሮው የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ ስለ አፍሪቃ ምንምን ጉዳዮች ተነሱ? – DW – 10 ጥር 2016

Play all audios:

Loading...

ፖለቲካአፍሪቃበዘንድሮው የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ ስለ አፍሪቃ ምንምን ጉዳዮች ተነሱ?10 ጥር 2016ዓርብ፣ ጥር 10 2016 በስዊዘርላንድ ዳቮስ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ5 ቀናት ሲካድ የነበረው የዓለም የምጣኔ ሀብት መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።ከ60 በላይ የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ 3 ሺህ የሚጠጉ


ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል በተባለው በዘንድሮው የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ፤ በተለይ ስለ አፍሪቃ ምንምን ጉዳዮች ተነሱ?


https://p.dw.com/p/4bTjcበስዊዘርላንድ ዳቮስ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ5 ቀናት ሲካድ የነበረው የዓለም የምጣኔ ሀብት መድረክ ከ60 በላይ የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ 3 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል ምስል፦ Denis Balibouse/REUTERSማስታወቂያየ2024 የዓለም


የምጣኔ ሀብት መድረክ To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio


 


«ታማኝነትን መልሶ መገንባት»በሚል መሪቃል ከጎርጎሪያኑ ጥር 15  ጀምሮ  ለ5  ተከታታይ ቀናት የተካሄደው  ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት መድረክ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል። በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው በዚህ መድረክ የጋዛ እና የዩክሬን አስከፊ ጦርነቶች ፣የሰው ሰራሽ አስተውሎት እመርታዎች


እና የፈጠረው ስጋት እንዲሁም የኮቪድ 19 የጤና እክል ጥሎት ያለፈው የኢኮኖሚ ድቀት እና ከፍተኛ የእዳ ቀውስ በመድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ናቸው።


መንግሥታትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ቢሊየነሮች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ባለሙያዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በዚህ መድረክ የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ እና የሩዋንዳው ፖል ካጋሜ ከአፍሪካ ቁልፍ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።በመድረኩ የተገኘው DW ዘጋቢ አሹቶሽ


ፓንዲ እንደሚለው በዚህ መድረክ የአፍሪቃ ተወካዮች የብድር እና የእዳ ቀውስን አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት እመርታ እና ስጋት በዘንድሮው የዓለም የምጣኔ ሀብት መድረክ የተነሳ አንዱ ጉዳይ ነውምስል፦ Gian Ehrenzeller/KEYSTONE/picture alliance


«በአፍሪካ ልዑካን እዚህ ለውይይት ከተነሱ አንዳንድ ዋና ዋና  ነጥቦች መካከል በአስቸጋሪው የዕዳ ቀውስ  እና  ከአበዳሪዎች ከሚመጡ ማንኛውም የእፎይታ መዘግየት ላይ ብዙ ትኩረት አለ። ያ ትልቅ ጉዳይ ነው።»የዳቮሱ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዛሬ በይፍ ተጀመረከዚህ በተጨማሪ የሃይል እጥረት ፣ የአየር


ንብረት ለውጥ እና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢኮኖሚ በማደግ ላይ ያሉ ብዙዎቹ የአፍሪቃ ሀገራት ከፍተኛ የብድር ጫና ውስጥ መሆናቸው በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።መድረኩን የተከታተለው ጋዜጠኛ ፓንዲ  እንደሚለው በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዘንድም የአፍሪቃ ሀገራት የዕዳ ቀውስ  ትኩረት የተሰጠው


ጉዳይ ነው።«የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት  በእርግጥ ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ካላቸው ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በከፍተኛ ጭንቀት እና ስጋት ውስጥ እንዳሉ ገልጿል። ኢትዮጵያ ያለፈው ታህሳስ  እዳ መክፈል ከማይችሉ የአፍሪቃ ሀገሮች ውስጥ ሆናለች።እናም አሁን፣ ሀገራቱ ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እና ምን


ያህል ማውጣት እንደሚችሉ በመሳሰሉ  የገንዘብ ጉዳዮች ላይ ይህ ስጋት አለ። ለእነሱ የብድር ወጭም እየጨመረ ነው።ስለዚህ ይህ አንዱ ጉዳይ ነው።»ከ60 በላይ የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከ2,800 በላይ ተሳታፊዎች በታደሙበት በዚህ  መድረክ ከፖለቲካ መሪዎች መካከል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን


፣የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን እና የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ይገኙበታል።በጋዛ ጦርነት ቁልፍ ባለድርሻ አካላት፣ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱራህማን አልታኒ ግጭቱን ማስቆም በሚቻልበት መንገድ ላይ


ተወያይተዋል።

ዩአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በዳቮሱ ጉባኤ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በዝግ መክረዋልምስል፦ Denis Balibouse/REUTERS


ዩአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በዝግ መክረዋል።ብሊንከን ከውይይቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በሩዋንዳ እና በኮንጎ መካከል ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅሰዋልትኩረት


በአፍሪቃ፣አፍሪቃ በዳቮስ፣የኮንጎ ጦርነት።


በቀጠሉት ሌሎች የአፍሪቃ ውይይቶችም የአህጉሪቱን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ተደራሽ የሚያደርግ የስራ እድል ስለመፍጠር እና የስነ ሕዝብ አወቃቀር ጉዳዮች ተነስተዋል። የዓለም ኤኮኖሚ መድረክ ጉባዔ ከዚህ በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም/UNDP/ እና በአፍሪካ መሪዎች ትብብር


የተመሰረተው የቲምቡክቶ  የሀብት ማሰባሰቢያ  መርሀ-ግብርም አንዱ የአፍሪቃ ጉዳይ ነበር።የአፍሪቃን የስራ ፈጠራ እና ጀማሪ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን ለመደገፍ የተቋቋመው ይህ መርሀ ግብር የዶቼ ቬለው ፓንዲ እንደሚገልፀው በአፍሪቃ ቢቢሊዮን በሚቆጠር ዶላር መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ዕቅድ አለው። «ዓላማው


በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር  የመዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ  ነው፣ ገንዘቡ መሰረት ያደረገው ኪጋሊ ላይ ነው።  ለዚህ ነው ፕሬዝዳንት ካጋሚ የሀብት ማሰባሰቡን ለመጀመር የሶስት ሚሊዮን ዶላር  እንደሚያዋጡ ያሳወቁት። ነገር ግን ገንዘቡ በተለያዩ ሀገራት ይሰራጫል


።»

በስዊዘርላንድ ዳቮስ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ5 ቀናት ሲካድ የነበረው የዓለም የምጣኔ ሀብት መድረክ ከ60 በላይ የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ 3 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታልምስል፦ Avalon/Photoshot/picture alliance


ያም ሆኖ የዳቮሱ ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት መድረክ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ቃል ቢገባም፤ በዝግጅቱ ወቅት የተሰጡ ሃሳቦች፣ ንግግሮች፣ ውይይቶች እና የተስፋ ቃሎች በመንግሥታት ላይ አስገዳጅ አንድምታ ስለሌላቸው ተፈፀሚነቱ ላይ ትችት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው።


በሌላ በኩል ለዚህ መድረክ አባልነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ለስልታዊ የሽርክና ክፍያ ያስፈልጋል።በዳቮስ ጉባኤ ላይ ለመገኘትም ተጨማሪ ወጪዎችን ይጠይቃል። ተቺዎች በጉባኤው ወቅት የሆቴሎች እና የምግብ ዋጋ ውድነትንም አጉልተው ያሳያሉ።


ፀሀይ ጫኔታምራት ዲንሳ


መጋቤ ምላሽዎን ይላኩልንየርስዎ መጋቤ ምልሽማስታወቂያ